እምነታችን
Orthodox Creed

እምነታችን
Orthodox Creed

እምነታችን

“ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደል የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም የሆነ የለም። በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለእኛ ስለሰው ስለ መዳኛችን ከሰማይ ወረደ። ከመንፈስ ቅዱስ የተነሣ ከቅድስት ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሆኖ በጰንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ። ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረም፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳት መጽሐፍት እንደ ተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ። ዳግመኛ ሕያዋንን ሙታንንም ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል። ለመንግሥስቱም ፍጻሜ የለውም። ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ፤ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ።

ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን። ኃጥያትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት አናምናለን። የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።”

DONATION

Thank you for your generous contribution to Lideta Mariam Ethiopian Orthodox Church.

  • ስጦታ / Offerings
  • አስራት / Tithe
  • የሕንጻ ግንባታ / Building Fund
  • የተለያየ ጉዳይ / Miscellaneous

TOP